top of page

ውጊያችን ከደምና ከስጋ ጋር አይደለም!

“በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤ የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን።” (2ቆሮ 10፡3-5) ክርስቲያኖችን ሁልጊዜም በውጊያ ላይ ነን። ይህ ውጊያ መጽሐፍ ቅዱሳችን እንደሚለን ከስጋና ከደም ጋር ሳይሆን መንፈሳዊ ውጊያ ነው። (“መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።” ኤፌ 6፡12) መንፈሳዊ ውጊያን ደግሞ የምንዋጋው በመንፈሳዊ እቃ ጦር ነው። መንፈሳዊ እቃ ጦራችን የጠላትን ምሽግ የመስበር ሃይል አለው። ብዙ ጊዜ የጠላት ፍላጻ ሲወረወርብን በተለያየ መንገድ ይገለጣል። እንዳንድ ጊዜ በህመም ሊገለጥ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ በባህሪ መረበሽ (በቁጣ፣ ንዴት፣ መደበት … ወዘተ) ሊገለጥ ይችላል። አንዳድ ጊዜ ግንኝነቶችን (በትዳር፣ ከልጆች ጋር፣ ከቤተሰብ ጋር፣ በስራ ቦታ) በማወክ ሊገለጥ ይችላል። እነኚህ ሁኔታዎች ሁልጊዜ ከጠላት ፍላጻ ብቻ ላይሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን በተለይም ከመንፈሳዊ አገልግሎቶች በኋላ እነኚህ ሁኔታዎች ሲከሰቱ ምንጫቸው የጠላት ውጊያ ሊሆን እንደሚችል መዘንጋት የለብንም። የጠላት ፍላጻ ወደኛ ሲወረወር የሶቱን “መ” ዎች መርህ በመጠቀም አሰራሩን ለመስበር እንችላለን። የመጀመሪያው “መ” መለየትን የሚወክል ነው። ለመንፈሳዊ ውጊያ የመጀመሪው እርምጃ መለየት ነው። ይህም የጠላት ፍላጻ እየተወረወረብን እንደሆነ መረዳትና መንቃት ነው። ሑለተኛው “መ” መቋቋምን የሚወክል ነው። አሰራሩን ከለየን በኋላ በመቀጠል ማድረግ ያለብን የጠላትን አሰራር መቋቋም ነው። የጥላትን ማንኛንም አሰራር መቋቋም የምንችለው ደግም የእግዚአብሔርን እቃ ጦር ሁሉ በመልበስ ነው። መጽሐፍ ሲለዚህ ጉዳይ ሲመክረን “የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ” ይለናል። (ኤፌ 6፡10) ጠላትን ለመቃወምና ስራውን ለማፍረስ የእግዚአብሔርን እቃ ጦር መልበስ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን እቃ ጦር ሁሉ ደግሞ ማንሳት ይኖርብናል። የሚገጋደደረንን የጠላት ሃይል ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም ለመቋቋምና ስራውን ለማፍረስ ስልጣን አለን። እግዚአብሔር በኛ ላይ ካሰበው በጎ ሃሳብ የሚጻረረውን ክፉ ሃሳብ ሁሉ ለማፍረስ የሚችል መንፈሳዊ የጦር እቃ አለን። ሶስተኛው “መ” የሚወክለው መደሰት የሚለውን ሃሳብ ነው። የጠላትን ሃሳብ ካፈረስን በኋላ ለአምላካችን ምስጋናን እያቀረብን መደሰት አለብን። መጽሐፍ ቅዱስ “ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ” ይለናል። በጌታ ሃሴት ስናደርግ ጠላት ራስ ምታት ይይዘዋል። ለዚህም ነው ቃሉ “ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ስለ ጠላትህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት” የሚለን። (መዝ. 8፡ 2) ወገኖቼ፦ የጠላትን ስራ አንስተውም። መለየትን፣ መቋቋምንና መደሰትን መርህ አድርገን እናፈርሰዋለን እንጂ። ክብር ለእግዚአብሔር ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን። አሜን!


Recent Posts
Archive
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
spotify-badge-button-listen-wh-BG.png
apple-podcasts-logo.jpg
Google-Podcasts-Badge.jpg
RadioPublicc.png
breaker.png
pocketcasts3.png
Anchor-Podcast-Logo.png

 

5850 N. Elston Avenue 

Chicago, Il 60646

10:00 AM TO 12:00 PM SUNDAY

7:00PM TO 9:00PM FRIDAY

  • Facebook Social Icon
  • Twitter Social Icon
  • Google+ Social Icon
  • YouTube Social  Icon
bottom of page