top of page

ልዩ መንፈስ - ፈጽሞ መከተል!

“ከእኔ ጋር የወጡት ወንድሞቼ ግን የሕዝቡን ልብ አቀለጡት፡ እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን

ፈጽሜ ተ ከተልሁ።” (ኢያሱ 14፡8)

የእግዚአብሔር ሰው ካሌብ ልዩ መንፈስ የነበረው ሰው ነው። ከዚህ በፊት

እንዳየነው ይህ የልዩነት የዕምነት መንፈስ ነው። ካሌብ በእግዚአብሔር ያመነ ሰው

ብቻ ሳይሆን እግዚአብሐርን ያመነ ሰው ነው። ይህ የልዩነት መንፈስ ደግሞ ደግሞ

በእግዚአብሔር የተፋ ቃል ላይ ፈጽሞ የመደገፍ መንፈስ እንደሆነም ተመልክተናል።

ዛሬ ደግሞ ይህ ልዩ መንፈስ እግዚአብሔርን ፈጽሞ የመከተል መንፈስ እንደሆነ

እንመለከታለን።

ካሌብ እግዚአብሔርን ፈጽሞ የተከተለ ሰው ነው። ይህንን ደግሞ ካሌብ

እራሱ “እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ ተከተልሁ” (ቁ8) በማለት

ያረጋግጥልናል። ይህ ደግሞ ካሌብ ሰለ እራሱ ምስክርነት የሰጠበት ጉዳይ ብቻ

ሳይሆን በሰውም በእግዚአብሔር ፊት የተገለጠ ነበር። ካሌብ እግዚአብሔርን

ፈጽሞ በመከተሉ የሚረግጠው ምድር ሁሉ ለእርሱና ለዘሩ ርስት እንደሚሆን ሙሴ

መስክሯል። (ቁ9) ሙሴ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሐርም እራሱ ካ ሌብ ፈጽሞ

እንደተከተለው መስክሮለታል። (ዘኅ. 32፡11-12 ፤ ዘዳ. 1፡36) ከዚህም የተነሳ

ትውልዱ ሁሉ በምድረበዳ ሲቀር ካሌብ ግን በሕይወት ቆይቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር

ገባ። ከብሮንንም ርስት አድርጎ ወሰደ። (ቁ.14)

ካሌብ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ነበር የተከተለው። እግዚአብሔርን

የተከተለው በሙሉ ልቡ ነበር። ሁለንተናውን ለእግዚአብሔር የሰጠ ሰው ነው።

ካሌብ ያልፍበት የነበረው ሁኔታና አካባቢው ልብን ሊከፍሉና ማመንታት ውስጥ

ሊያስገቡ የሚችሉ ነበሩ። እርሱ ግን ከአስሩ ወገኖቹ ጋር ለአሰሳ በወጣ ጊዜ

የተሰለፈው ከብዙሃኑ ሃሳብ ጋር ሳይሆን ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር ነበር።

አብረውት የወጡት አስሩን አልተከተለም። እንዲሁም ተስፋ የቆረጠውንም ሕዝብ

አልተከተለም። እርሱ እግዚአብሔርን ተከተለ።

መከተል የእራስን ሃሳብ በ እግዚአብሔር ሃሳብ መጠቅለልን የሚጠይቅ ነው።

በፈቃዱ ውስጥ መግባትን ይጠይቃል። ጌታችንም በወንጌላት ያስተማረን “እኔን

መከተል የሚወድ እራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ” በማለት ነው።

(ማቴ. 16፡24) የተጠራነው ጌታን እንድንከተል ነው። የራሳችንን ፍቃድ

እያገለገልን ጌታን ለመከተል አንችልም። መከተል መስቀልንም መሸከም

ይጠይቃል። ነገር ግን ጌታን በፍጹም ልብ ስንከተል እንደ ካሌብ ከመልካም

ነገር አንጎድልም። በህይወት እንኖራለን ፤ ርስታችንን እንወርሳለን ፤ በተስፋው

ቃል ላይ እንደገፋለን ፤ ሽምግልነታችን በዘይት ይለመልማል። አሜን!


 
Recent Posts
Archive
Search By Tags
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
spotify-badge-button-listen-wh-BG.png
apple-podcasts-logo.jpg
Google-Podcasts-Badge.jpg
RadioPublicc.png
breaker.png
pocketcasts3.png
Anchor-Podcast-Logo.png

 

5850 N. Elston Avenue 

Chicago, Il 60646

10:00 AM TO 12:00 PM SUNDAY

7:00PM TO 9:00PM FRIDAY

  • Facebook Social Icon
  • Twitter Social Icon
  • Google+ Social Icon
  • YouTube Social  Icon
bottom of page