top of page

ሕብረት

እንደ አባቶች ፈለግ እንደ ሐዋሪያት፣

በፊቱ እንደ ተጉት በአንድ ልብ ጸሎት፣

የመንፈስን ሙላት እንደ ተቀበሉት፣

በግልጽ እንደ ናኙት የወንጌሉን ብስራት፣

በኃይል እንደ ሮጡት ለገባቸው እውነት፣

እንዳለቆማቸው ሰይፍና እስራት፣

እንደ ገሰገሱት በአላማ ጽናት፣

እኛም ስንጋጠም ስንቆም በሕብረት፣ ልዩነት ደብዝዞ ሲፈካ አንድነት፣ ለአምላክ ደስ የሚያሰኝ የሚያውድ መስዋዕት፣

በመንፈስ ተሳስረን ስናቀርብ በውበት፣

ሽታችን ይወጣል ይማርካል ነፍሳት። ከራስ እንደ ’ሚወርድ እንደ አሮን ዘይት፣

ይገለጣል በኛ የክርስቶስ ሕይወት፣ ጨለማን የሚገፍ የብርሃን ፍካት።

እኛ ስንያያዝ የአንድ አባት ልጆች፣ ለዘላለም ንጉስ ሲከፈቱ ልቦች፣ እንደ አሴር በረከት ዘይት ሲጠልቁ እግሮች፣

በኃይል እንቆማለን ሆነን ምስክሮች፣

ፊታችን አይቆሙም የገሃነብ ደጆች።


Recent Posts
Archive
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
bottom of page