top of page

መንፈስ ቅዱስና የእግዚአብሔር ፍቅር።

የእግዚአብሔር ፍቅር በልባቸን የፈሰሰው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው። በሮሜ 5:5 ላይ የእግዚአብሔር ቃል “በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም” ይለናል። “ፈሰሰ” የሚለው ቃል የእግዚአብሔር ፍቅር ያለገደብ ወደ እኛ እንደመጣ የሚገለጽ ነው። ለኛ የተገለጠው የእግዚአብሔር ፍቅር ወደር የለውም። የዚህን ፍቅር ጥልቀት ለመግለጽ ሐዋሪያው ጳውሎስ “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል” (ሮሜ 5:8) ይለናል። የእግዚአብሔር ፍቅር በኛ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ አይደለም። ልጁን ለኛ እንዲሞት የፈቀደው እኛ ገና በሐጢያት ሳለን እና ፈጽሞ የማይገባን ሆነን ነው። የዚህ ፍቅር ምንጭ እግዚአብሔር እራሱ ነው። እግዚአብሄር ከርሱ በወጣው ፍቅር ወዶናል። ዛሬም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆንም እግዚአብሔር ይወደናል። የኛ መንፈሳዊ መረዳት እና የሕይወት ምልልስ እግዚአብሔር ለኛ ያለውን የፍቅር ደረጃ አይወስንም። ይህ ፍቅር ለሰው ልጅ ሁሉ የተገለጠ ነው። ክርስቶስ ለአለም ሁሉ (ለሰው ዘር ሁሉ) ነው የሞተው። የኛ ድርሻ ወደ እግዚአብሔር የፍቅር ጥሪ በመታዘዝ መግባት ነው።

እግዚአብሔር ስለወደደን ተስፋን ሰጥቶናል። ይህ ተስፋ ደግሞ ይሚያሳፍር ተስፋ አይደለም። የሚፈጸመም፤ የሚሆን ተስፋ ነው። ለዚህ ደግሞ ያለን ዋስትና የእግዚአብሔር ፍቅር ነው። እግዚአብሔር አንድ ልጁን በመስጠንት ለኛ ያለውን ፍቅር ያውም እኛ ገና ኃጢያተኞች ሳለን ስለገለጸ የሰጠንን ተስፋ ሁሉ እንደሚፈጽምልን እርግጠኞች ነን። በእርግጥ ቃሉ እንደሚያስተምረን “ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?” (ሮሜ 8፡ 32) በእርግጥ ልጁን የሰጠን ጌታ ከልጁ ጋር ሁሉን እንደሚሰጠን እናምናለን።

ለኛ የተገለጠው የእግዚአብሔርን ፍቅር ለመረዳት የሚንችለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ብቻ ነው። ስለዚህ ጉዳይ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን “ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ” እጸልያለሁ ይላል። ፍቅሩ ጥልቅ ነው። የመጨረሻ አዘዕቅት ውስጥ ያለነውን ይደርሳል። ከፍታው እስከ ሰማየ ሰማያት ይደርሳል። ለሁሉም የሚበቃ ሁሉንም ለማቀፍ የሚችል ነው ስፋቱ። የክርስቶስን ፍቅር በአእሞሮአችን ተረድተን የሚንጨርሰው አይደለም። ከአእሞሮ በላይ የሆነ ነውና ከመታወቅ ያልፋል። የክርስቶስን ፍቅር እናውቀው ዘንድ ኃይልን የሚሰጠን መንፈስ ቅዱስ ነው። መንፈስ ቅዱስ ይህ ፍቅር በልባችን ፈሶ እንዳለ ያሳውቀናል። በዚህ ፍቅር ውስጥም ለመመላለስ እንድችል አቅም ይሰጠናል።

የእግዚአብሔርን ፍቅር ስንረዳ ለተጠራንበት መጠራት እንደሚገባ እንድንኖር ኃይል እናገኛለን። እግዚአብሔርንም ለማገልገል ኃይል እናገኛለን። ስለዚህ ነው ሐዋሪያው ጳውሎስ “የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል” የሚለን። (2ቆሮ. 5:14) ፍቅሩን ከተረዳን የሚያቆመን ምንም ነገር አይኖርም። ለዚህ ነው ጌታ ኢየሱስ ከፍቅሩ ተነስተን እንድናገለግለው ያስተማረን። ከወደድነው ራሳችንን ቅዱስ መስዋዕት አድርገን እናቀርብለታለን፣ በትጋትና በግለት እናገለግለዋለን፣ እርሱ የወደዳቸውን እንወዳለን። ወገኖቼ፦ መንፈስ ቅዱስ ለኛ የተገለጠውን የክርስቶስን ፍቅር ተረድተን በፍቅሩ እንድኖርና እንድንመላለስ ኃይልን ይሰጠናል። አሜን!


Recent Posts
Archive
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
spotify-badge-button-listen-wh-BG.png
apple-podcasts-logo.jpg
Google-Podcasts-Badge.jpg
RadioPublicc.png
breaker.png
pocketcasts3.png
Anchor-Podcast-Logo.png

 

5850 N. Elston Avenue 

Chicago, Il 60646

10:00 AM TO 12:00 PM SUNDAY

7:00PM TO 9:00PM FRIDAY

  • Facebook Social Icon
  • Twitter Social Icon
  • Google+ Social Icon
  • YouTube Social  Icon
bottom of page