top of page

እግዚአብሔር እረኛዬ ነው -- ጽዋዬም የተረፈ ነው።

ንጉስ ዳዊት በመዝሙር 23 ከእግዚአብሔር እረኝነት ጋር አያይዞ እግዚአብሔር የተትረፈረፈን ሕይወት የሚሰጥ አምላክ እንደሆነ ይቀኛል። ይህንን ሃሳብ የሚገልጸው “ጽዋዬም የተረፈ ነው” በማለት ነው። በዚህ ስፍራ አግባብ “ጽዋዬ” በማለት ዳዊት የሚገልጸው ከእግዚአብሔር የተቀበለውን በረከትና ሕይወት ነው። በሌላም ስፍራ እግዚአብሔር እድል ፋንታው መሆኑን በመግለጽ “እግዚአብሔር የርስቴ እድል ፈንታና ጽዋዬ ነው፥ ዕጣዬንም የምታጠና አንተ ነህ” በማለት ያመሰግናል (መዝ. 16:5)። እግዚአብሔር ለዳዊት የሰጠው ጽዋ የሞላ ብቻ ሳይሆን ሞልቶ የተረፈ ነው።

እግዚአብሔር በክርስቶስ የሰጠን ሕይወት እንዲሁ የተትረፈረፈ ነው። ጌታ ኢየሱስ ይህንን ጉዳይ በአዲስ ኪዳን ሲያስተምር “እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ” (ዮሐ. 10:10) በማለት ገልጾታል። ጌታችን ይህንን የተናገረው ከእረኝንቱ ጋር አያይዞ ነው። ዳዊት በመዝሙሩ እግዚአብሔር እረኛዬ ስለሆነ የተትረፈረፈ ሕይወት ይሰጠኛል እንዳለ ሁሉ ጌታችን ደግሞ እረኛ ለሆነላቸው በጎቹ የሚበዛ ሕይወትን እንደሚሰጣቸው አስተምሯል። በተለይም ይህንን ጌታችን የገለጸው ሌባው (ማለትም ዳቢሎስ) ከሚያደርገው ጋር በማነጻጸር ነው። ሌባው ዳቢሎስ “ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም” (የሐ. 10:10)። ሌባው እየጨመረ ለሚሄድ ክፋት ይመጣል። ማለትም መጀመሪያ በማታለል ይሰርቃል፣ ከዚያም የሰረቀውን ይገድለዋል መጨረሻው ደግሞ የዘላለም ጥፋት ይሆናል። በአንጻሩ ጌታችን ደግሞ እርሱ የሕይወት እራስ ስለሆነ ከሞት ወደ ሕይወት አሻግሮ ሕይወትን ይሰጣል። ይህ ሕይወት ደግሞ እየበዛና እየጨመረ ይሄዳል።

እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለው አላማ መብዛት ነው። የእግዚአብሔር ነገር የሚበዛና የሚያሸንፍ እንደሆነ ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ለሚደገፉት ያለው አላማም መብዛት ነው። ገና በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው ሰው እንዲበዛና ፍሬያማ እንዲሆን ባርኮታል (ዘፍ. 1:28)። ይህ መብዛት በቁጥር ማደግን ብቻ የሚገልጽ ሳይሆን በነገር ሁሉ ተጽንኖ አምጪ መሆንን የሚያሳይ ነው። በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሁልጊዜ ኃይላቸው እየታደሰ ይሄዳል እንጂ አይደክሙም (ኢሳ. 40:31)። እንዲሁም ቃሉ “የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል” እንደሚል (ምሳሌ 4:18) ብርሃናቸው እየጨመረ ይሄዳል። የእግዚአብሔር ሰዎች የተመላሱት በዚህ መርህ ነው። ቃሉ ስለ አሴር በረከት “ጫማህ ብረትና ናስ ይሆናል፤ እንደ ዕድሜህ እንዲሁ ኃይልህ ይሆናል” ይላል (ዘዳ. 33:25)። አሴር ጫማው የሚያደቅ ነው። እድሜው ሲጨምር ደግሞ ኃይሉ ይጨምራል። ዳዊትም በሌላ መዝሙር “በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው... ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ” (መዝ 84:4፣7) በማለት እግዚአብሔር የሰጠን ሕይወት የተትረፈረፈ እንደሆነ ዘምሯል። ካሌብም “ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬ ጕልበታም ነኝ፤ ጕልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው” (ኢያሱ 14:21) በማለት በሚጨምር የመንፈስ ብርታት እንደኖረ በእመነት ተናግሯል።

ወገኖቼ፦ ዘማሪው “የኔ ነገር ይበዛል” እንዳለ በክርስቶስ ያለን ሕይወት እየበዛ፣ እያደገ፣ እየተትረፈረፈ የሚሄድ እንጂ የሚያንስ አይደለም። በኛ ያለው መንፈስ ቅዱስ ተጽኖው በየጊዜው እየጨመረ የሚሄድ ነው። (ሕዝ. 47) የተጠማን የነበርን እኛ ወደ ክርስቶስ መጥተን ወንዞች የሚፈልቁብን ሆነናል። ጽዋችን የተረፈ ነው። የእግዚአብሔር ስም ለዘላለም የተባረክ ይሁን። አሜን!


Recent Posts
Archive
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
spotify-badge-button-listen-wh-BG.png
apple-podcasts-logo.jpg
Google-Podcasts-Badge.jpg
RadioPublicc.png
breaker.png
pocketcasts3.png
Anchor-Podcast-Logo.png

 

5850 N. Elston Avenue 

Chicago, Il 60646

10:00 AM TO 12:00 PM SUNDAY

7:00PM TO 9:00PM FRIDAY

  • Facebook Social Icon
  • Twitter Social Icon
  • Google+ Social Icon
  • YouTube Social  Icon
bottom of page