top of page

በማህበራዊ ሚድያ የሚሠራጭ ድምጽ መለየት፤ ሃላፊነት የተሞላ አጠቃቀምና መወሰድ ያለበት ጥንቃቄ

ባለንበት ጊዜ በተለይም በ COVID 19 ወረርሽኝ የተነሳ በአብዛኛው ቤት ውስጥ ተከተን ባለንበት በዚህ ወቅት፤ የተለያየ ድምጽ፣ አስተሳሰብ፣ ጩኸት፣ አመለካከት እና ፕሮፓጋንዳ የምንሰማበት አጋጣሚ ሰፊ ነው። በተለይም የመሀበራዊ ትስስሮሹ ከመቼውም በላይ እስከ ጓዳችን ዘልቆ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ በየትኛውመ የዓለም ክፍል የተፈጠረ ኮሽታ የምንሰማበትና የምናይበት አጋጣሚ ቅጽበታዊ ሆኗል። የመሃበራዊ ሚዲያ ሲባል ፌስ ቡክ፣ ዩ ቲዪብ፣ ትዊተር፣ ቫይበር፣ ሃንግ አውት ፣ ጎልጉል ወዘተርፈ ያካተተ ነው። ስለ ማህበራዊ ሚዲያ እና ስለ ጥቅሙ በዙ ስለተባለ፣ ለአንባቢያን የሚተው ይሆናል። ሆኖም ግን በመሃበራዊ ሚዲያ የምንሰማውን ድምጽ እንዴት መለየት እንዳለብን ብንጠይቅ ተገቢ ጥያቄ ይሆናል። ለጥቆ፣ እንደ አማኝ፣ እንደ ባለአምሮና አስተዋይ ሰው አቀራረባችን፣ እይታችን ምን መሆን አለበት? መጽሃፍ ቅዱሥ የምንሰማውን ድምጽ እንድንመረምር ይናገራል። ስለዚህም የምንሰማውን ድምጽ ወዲያው አምነን ውስጣችን ከመስተጋባቱ በፊት፣ ቀጥሎ ያሉትን ጥያቄዎች ብንጠይቅ ተገቢ ነው። ተናጋሪው ማነው? ሥለ ምንድነው የሚናገረው? የንግግሩ ጭብጥ ሃሳብ ምንድነው? ስለ እውነትነቱ ምን ማረጋገጫ አለ? ንግግሩን መስማቱ እንደአማኝ የሚያስገኘው ጥቅም ምንድነው? ከእግዚአብሄር ቃል አንፃር እንዴት ይታያል? ዳግም ሊሰማስ ይገባዋል? ጊዜ አላቂ ሐብት ሥለመሆኑ ልብ ልንል ይገባል። የሰው ልጅ እድሜ በመፅሐፍ ቅዱስ እንደተነገረው ከሰማኒያ ካለፈ ድካም መሆኑ ነው። በማህበራዊ ሚድያ የሚኖረን ጊዜ ከዚሁ እድሜያችን ላይ ተቆንጥሮ የሚወሰድ ነው። ሥለዚህም ያለ አግባብ እንዳናጠፋው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ለምስሌ፣ ስብከት ማዳመጡ መልካም ነው፣ ከዚያም ብዙ እንማራለን፤ ሆኖም በግላችን መጽሐፍ ቅዱስን ብናነብ እግዚአብሔር ለልባችን ይናገረናል። እንዲሁም ደጋፊ መጽሃፍትን የማንበብ ልምዳችን ቢዳብር ከመሃበራዊ ሚዲያ የበለጠ ጠቀሜታ ይኖረዋል።

ሌላው፤ ውስጥን/እራሥን ለማዳመጥ ጊዜ መውሰድ አለመቻል፤ በመሃበራዊ ሚዲያ ዘመን የሚታይ ችግር ነው። ምክንያቱም የተናገረ ሁሉ እንደ አዋቂ የሚሚቆጠር በመሆኑ ነው። እስከመቼስ አእምሮአችንና ሐሳባችንን ባላዋቂ ተናጋሪዎች የተሳሳተ ዲስኩር እያጨቅን እንቀጥላለን? እግዚአብሄር የልብ አምላክ ሥለሆነ ለልብ ይናገራል። ብንዘጋጅ የጥሞና እና የፀሎት ጊዜ ቢኖረን እግዚአብሄር ሊናገረን ዝግጁ ነው። ከመሓበራዊ ሚዲያ አሊያም ከሶስተኛ ወገን ከመሥማት ከምንጩ ከእግዚአብሄር ቃል መስማቱ ተመራጭ ነው። እኛ ከተዘጋጀን፤ ሁል ጊዜ እግዚአብሄር ሊናገረን ዝግጁ ነው።

ከማህበራዊ ሚድያ የሰማነውን ሁሉ ለሌላ ወገን ከማስተላለፍ እንቆጠብ። በተለይም እውነትነቱ ያልተረጋገጠ መረጃ ወይም አሉባልታ በማወቅ ሆነ ሳናውቅ ሰናሠራጭ የአመፅ ልጅ የሆነውን ዲያብሎሥን እያገለገልን እንደሆነ ልብ ልንል ይገባል። የአመጽ ወሬን ማስተላለፍ ሲባል ሼር ወይም ላይክ ማድረግን ይጨምራል። ሐላፋነት ሊሰማን ይገባል። ሼር፣ ላይክ ያደረግነው መረጃ ምናልባት ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ቢሆንስ? ሥለዚህ፣ ቀላል የሚመስለው ድርጊታችን በእግዚአብሔር ፊት የሚያስጠይቅ ይሆናል ። ዋጋ እንከፍልበታለን።

ማህበራዊ ሚዲያ ስንገለገልበት ፤ መወሰድ ካለበት ጥንቃቄዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል። ሥሜታዊነትን ማስወገድ፤ ውሳኔ ጋር ስንደርስ መረጃው ከሚፈጥርብን የስሜት መዋዠቅ ማለትም ደስታ ፣ሀዘን ፣ ወይም ቁጣ ውስጥ ሆነን ከድምዳሜ ከመድረስ መቆጠብ ። ሥሜታችን እሥኪሰክን ውሳኔያችንን ብናዘገይ ከተሳሳተ ውሳኔ እንዳንደርስ ሊረዳን ይችላል። መገምገም፣ ማሰላሰል፤ እንደባለአእምሮ የሰማነውን ወይም ያየነውን መረጃ/ዲስኩር ጊዜ ወስደን ማሰላሰል ያስፈልጋል። ምክንያቱም አእምሮ የተፈጠረው ለዚሁ አላማ በመሆኑ ነው። ትንቢትንም እነኳ እንድንመረምር ታዘናል። በየዋህነት የተነገረው ሁሉ እውነት እንደሆነ መቀበል፤ እንዲሁም እውነተኛ መልእክት ተነግሮ ሳለ አለማስተዋል ሁሉቱም ከስተት የሚጥል ነው። መስማት የተገባንን እንስማ፤ መስማትም ከእግዚአብሄር ቃል ከእንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ስለዚህ የተነገረውን ሁሉ ለመስማት የተደረገውን ሁሉ ለማየት ከፈለግን ጊዜውም ሆነ ጉልበቱም አይኖረንም። መምረጥ ያስፈልጋል። ከራሳችን፣ ከቤተሰባችን፣ከቤተክርስቲያንና ከእእግዚአብሄር መንግሥት ጋር ግንኙነት ያለው፤ እንዲሁም አሻራ ልናሳርፍ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ብናተኩር ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ በመጠቀም ውጤታማ እንሆናለን።

ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን፤ ከልዩነት አንድነትን፤ ከፀብ ይልቅ አርቅ ላይ ማተኮሩ መንፈሳዊነት ብቻ ሳይሆን የሞራል ግዴታ እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባል። ከእግዚአብሔር ቃል አንፃር የሰማነውን መመርመር ፤ የተነገረው ነገር ጭብጥ እና ከመፅሀፍ ቅዱስ ሀሳብ ጋር ልዩነት ወይም አንድነት ካለው ማነጻፀሩ ተገቢ ነው። ከትክክለኛ ድምዳሜ ለመድረስም ያግዛል ።

ሲጠቃለል ጊዜያችንን ሊለካ በሚችል ሥራ ላይ ብናሳልፍ መልካም ይሆናል። በዘፍጥረት መፅሐፍ እንደሚናገረው፤ እግዚአብሔር ሰውን ከፈጠረ ፣ የሚታዩና የሚጨበጡ እንደብርሃንና ውሀ ያሉትን እንዲሆኑ ካደረገ በኋላ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። እኛም የሚዳሰስ ፣የሚታይ፣ የሚጨበጥ እና አወንታዊ ውጤት ያለው ስራ ላይ ብናተኩር ከእግዚአብሔር ቃል አንፃር የተደገፈ ነው። ማህበራዊ ሚዲያን በዚሁ አቀራረብ ብንገለገልበት መልካም ይሆንልናል።


Recent Posts
Archive
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
spotify-badge-button-listen-wh-BG.png
apple-podcasts-logo.jpg
Google-Podcasts-Badge.jpg
RadioPublicc.png
breaker.png
pocketcasts3.png
Anchor-Podcast-Logo.png

 

5850 N. Elston Avenue 

Chicago, Il 60646

10:00 AM TO 12:00 PM SUNDAY

7:00PM TO 9:00PM FRIDAY

  • Facebook Social Icon
  • Twitter Social Icon
  • Google+ Social Icon
  • YouTube Social  Icon
bottom of page